Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ ዜና የቅርብ ዜናዎች አመልድ 11ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በድምቀት አካሄደ

Hi Slider ID 1

        አመልድ 11 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በድምቀት አካሄደ

አመልድ 11 መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን መጋቢት 19 ቀን 2009 . በባህርዳር ከተማ ግራንድ ሪዞርትና ስፓ መሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት አካሄደ፡፡ በጉባኤው ላይ የፌደራልና የክልል መስሪያ ቤት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና አመራሮች፣ የልማት ድርጅቶች ተወካዮች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የአመልድ ፕሮጀክት ተጠቃሚ አርሶ አደሮች፣ የቦርድና ስራ አመራር ኮሚቴ አባላት በጉባኤ አባልነትና ተሳታፊነት ተካፍለዋል፡፡

              2017 meeeting4

የእለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር በጉባኤ መክፈቻ ንግግራቸዉ እንዳብራሩትአመልድ ከአከናወናቸዉ የልማት ስራዎች አኳያ ሲታይ የመልካም ተሞክሮዎች /ቤት ነው ቢባል ማጋነን አይደለም፡፡. በተለይም በንጹህ መጠጥ ዉሃና መስኖ ልማት፣ በደን ልማት፣ በአፈርና ዉሃ እቀባ በክልላችን አመልድ ያከናወናቸዉ የልማት ስራዎች አረንጓዴ የምስክር ሀዉልቶች ናቸው፡፡ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል ክቡር አቶ አህመድ አብተው የአመልድ ቦርድ ሊቀመንበር በእንን ደህና መጣችሁ ንግግራቸዉ እንዳስረዱት አመልድ አኩሪ ስኬቶችን እንዲያስመዘግብ ያደረገዉ ቁልፍ ሚስጥር ከማኅበረሰቡ፣ ከመንግስት፤ ከረጅ-ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅትና በትብብር መስራት በመቻሉ ነዉ ሲሉ አስረድተዋል፡፡

            2017 meeting

የተከበሩ / አምላኩ አስረስ የአመልድ ዋና ዳይሬክተር በበኩላቸዉ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በአለፉት 32 የልማትና ስኬት አመታት አመልድ 5 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸው ... 2016 ብቻ 32 ለጋሽ ድርጅቶች፣ የልማት አጋሮቹና ከተጠቃሚዉ ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት 64 ወረዳዎች 65 የተቀናጁ የልማት ፕሮጀክቶችን በመተግበር ወደ 1.7 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

በመቀጠልም ጉባኤዉ በዶ/ አምላኩ አስረስ በቀረበው 2014-16 የአመልድ ስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ አጽድቋል፡፡ በመሆኑም የቀረበው ሪፖርት የሶስት አመት ሪፖርትና 2016 አመታዊ በጀት ሪፖርትን ያካተተ መሆኑን አረጋግጦ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ አጽድቆታል፡፡

ጉባኤዉ በማስከተል የተወያየዉ በድርጅቱ ኦዲት ሪፖርት ላይ ነው፡፡ ጉባኤዉ በዘመድሁንና ኩባንያዉ የተባለ የዉጭ ኦዲት ፊርም ተወካይ አማካኝነት የቀረበውን 2016 የአመልድ ኦዲት ሪፖርት መርምሯል፡፡ አዲት ሪፖርቱ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን ሪፖርቱ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለዉ የሂሳብ አሰራር መሰረት የተሰራ እንከን የለሽ መሆኑን በማረጋገጥ ጉባኤው በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

ሶስተኛዉ የጉባኤው አጀንዳ የተመለከተው .. 2017 ዓመት የስራና በጀት እቅድ ሲሆን በኢንተርፕራይዝ ልማት /ዋና ዳይሬክተር በአቶ ሰጥቷል ደባልቄ በገለጻ በዝርዝር ቀርቧል፡፡ ጉባኤው በእቅዱና በጀቱ ላይ ከተወያዬ በኃላ እቅዱ በክልሉ ለዉጥ ሊያመጣ የሚችል መሆኑን በመቀበል በሙሉ ድምጽ ተቀብሎ አጽድቆታል፡፡

በመጨረሻም በአለፉት ሁለት የምርጫ ዘመናት 8 ዓመታት ያገለገሉ የስራ አመራር ቦርድ አባላትንና የጠቅላላ ጉባኤ አመራር አባላትን የአገልግሎት ጊዜያቸው የተጠናቀቀ በመሆኑ በምስጋና ሸኝቶ አዲስ ሶስት ጠቅላላ ጉባኤ አመራር አባላትና ከዘጠኙ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዉስጥ ስምንቱን የመረጠ ሲሆን ዘጠነኛዉ አባል ወደፊት በሙያዉ ወይንም በአስፈላጊነቱ የታመነበትን ቦርዱ መርጦ እንዲሰይም ተወስኖ ጠቅላላ ጉባኤው በእለቱ 1130 ላይ በስኬት ተጠናቅቋል፡፡

 
ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today9
Week451
All71986

Currently are 18 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?