Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ ዜና የቅርብ ዜናዎች በአመልድ የሚተገበር የጆን ሪግ መጠጥ ውሃ፣ የግልና አካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

Hi Slider ID 1

   በአመልድ የሚተገበር የጆን ሪግ መጠጥ ውሃ፣ የግልና አካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
(
ጥር 13 ቀን 2009 . -/ማርቆስ)
    

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) በቪቫ ኮን አጉዋ አመቻችነት ከዌልት ሃንገር ሂልፍ ከተሰኘ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ባገኘው 220 ሚሊዮን ብር በምስራቅ ጎጃም ዞን የሚገኙ 5 ወረዳዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጆን ሪግ መጠጥ ውሃ፣ የግልና አካባቢ ንጽህና ፕሮጀክት የትውውቅ አውደ-ጥናት አካሂዷል፡፡     

ፕሮጀክቱ በጎዛምን፣ ስናን፣ አነደድ ደብረ ኤልያስ እና ማቻክል ወረዳዎች 8 ዓመታት (2009- 2016) የሚተገበር ሲሆን 280 ሺህ በላይ ህጻናትን፣ ሴቶችንና ወንዶችን ተጠቃሚ የሚያደርና በአመልድ የመጠጥ ውሃ፣ ንጽህናና ስነ-ጤና ስራዎች በከፍተኛ በጀትና ብዙ ቁጥር ተገልጿል፡፡

            WASH

በትውውቅ ፕሮግራሙ የአመልድ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩና የፕሮግራሞች ሃላፊ አቶ ደጀኔ ምንልኩ እንደገለጹት የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) በክልሉ ውስጥ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን በማከናወን ለድሃው ማህበረሰብ ኑሮ መሻሻል ያላሰለሰ ጥረት የሚያደርግ የክልሉ የረጅም ጊዜ አጋር የልማት ድርጅት ነው ብለዋል፡፡ 
ድርጅቱ 30 ዓመታት በላይ የምግብ ዋስትና መታጣት ባለባቸውና የከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ፣ ከጥገኝነት ተላቀው በምግብ ሰብል ራሳቸውን እንዲችሉ ከማድረጉም በላይ ጥሪት/ሃብት እንዲያፈሩ አስችሏቸዋል፡፡

አመልድ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎችን ለመቋቋም የሚደግፉ ስራዎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የሰብል፣ እንስሳትና አካባቢ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማስፋፋት አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች ኑሮ እንዲሻሻል ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡ ከዚህ ባሻገር ተጨማሪ የእርሻ መሬት የሚፈጥሩ የጠረጴዛ እርከን፣ የተፋሰስ ልማት፣ የአፈርና ውሃ ጥበቃ እንዲሁም የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና መስኖ ልማት ስራዎችን ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በበኩላቸው አንጋፋው የክልሉ የልማት አቅም የሆነው አመልድ ካሁንቀደም በዞኑ የሰራቸው የመስኖ፣ መንገድ፣ ድልድዮችና ንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማት ጥሩ ማሳያዎች እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

             wash3
ዋና አስተዳዳሪው አመልድ ከቪቫ ኮን አጉዋ እና ዌልት ሃንገር ሂልፍ ህብረተሰቡን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አድንቀው ለፕሮጀክቱ ውጤታማነት የዞንና ወረዳ አስተዳደር፣ ውሃ፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ሴቶችና ህጻናት እና የጤና መስሪያ ቤቶች በሙሉ በቅንጅት ተግተው እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡

በአውደ-ጥናቱ ማጠናቀቂያ ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የምስራቅ ጎጃም ዞንና ወረዳ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ ከዌልት ሃንገር ሂልፍና አመልድ ተሳታፊዎች ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ በውጤታማነት ተጠናቅቋል፡

Last Updated (Monday, 10 July 2017 10:41)

 
ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today6
Week448
All71983

Currently are 3 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?