Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ ዜና የቅርብ ዜናዎች አመልድ የ2016 የአውሮፓ ማኅበር ጥራት ምርምር (ESQR) የጥራት ተሸላሚ ሆነ!

            አመልድ የ2016 የአውሮፓማኅበር ጥራት ምርምር (ESQR) የጥራትተሸላሚ ሆነ!

                dra1

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) በኢትዮጵያ የአማራ ክልል ውስጥ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ህይወታቸውን የሚገፉ የህብረተሰብ ክፍሎች የምግብ ዋስትናቸው ተረጋግጦ፣ ጥሪት እንዲያፈሩና የኑሮ ዘይቤያቸው እንዲለወጥ ጉልህ አስዋጽኦ አበርክቷል፡፡ ድርጅቱ በአሁኑ ሰዓት በሚያከናውናቸው መጠነ-ሰፊ የልማት እንቅስቃሴዎችና በአመራር ጥራት ዓለምአቀፍ  ሽልማት አግኝቷል፡፡ የአውሮፓ ማኅበር ጥራት ምርምር(ESQR) ዘላቂ ልማት እንቅስቃሴዎች የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማትና ድርጅቶች በርሊን (ጀርመን) ውስጥሰኞ, ታኅሣሥ 12, 2016 ባካሄደው የሽልማት ስነ-ስርዓት አመልድን የዚህ ልዩ ተሸላሚ አድርጎታል፡፡ 

በላውሳኔ (ስዊዘርላንድ) ላይ የተመሠረተው የአውሮፓ ማኅበር ጥራት ምርምር (ESQR), የጥራት ሥራ አመራር ላይ ስትራቴጂያዊ ጥያቄዎች የሚመልሱና ጥሩ የጥራት ሥራ አመራር ዘዴዎችን የሚተገብሩ ተቋማትን ዓለም አቀፍ መድረክ በማዘጋጀት በየዓመቱ ይሸልማል፡፡ የሽልማቱ ዓላማ ጥራት ባህል እንዲሆንና  ቀጣይነት ያለው መሻሻል እንዲሰፍን ለማበረታታት የአውሮፓ ማኅበር ጥራት ምርምር (ESQR) ተግቶ ይሰራል፡፡

የአውሮፓ ማኅበር ጥራት ምርምር (ESQR) የጥራት ሥራ አመራር ስልቶችን የተገበሩና ልዩ ስኬት ያስመዘገቡትን የተመረጡ ድርጅቶችየሕዝብ አስተዳደሮች እና ኩባንያዎች ከአውሮፓ፣ እስያ፣ አሜሪካአፍሪካ እና አውስትራሊያ ውስጥ በማወዳደር የጥራት ሽልማት እውቅና ይሰጣል፡፡ ድርጅታችን አመልድም በተጎናጸፈው ልዩ ስኬት ዓለምአቀፍ ተሸላሚ በመሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ!!

 
ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today3
Week118
All79216

Currently are 23 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?