Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ ስለ አመልድ የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

                            ዋና ዳይሬክተ መልዕክት

DrAlemayehu

ለተከበራችሁ የክልላችን ብሎም የአገራችን ህዝቦች፣ ለጋሽ ድርጅቶች፣ አጋር አካላት እንዲሁም የፕሮጀክት ተጠቃሚዎችና ለድርጅቱ ሰራተኞች እንኳን ለአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አደረሳችሁ!

በድርጅቱ 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ተሳታፊ በመሆኔና ይህንን መልእክት ማስተላለፍ በመቻሌ    በአመልድ ማኔጅመንት፣ሰራተኞችና በራሴ ስም የተሰማኝን ደስታመግለጽ እወዳለሁ፡፡

አመልድ 1976 ዓ.ም ከዛሬ 35 ዓመታት በፊት ሲቋቋም በወቅቱ በሰሜን ምስራቅ የአገራችን ክፍል በየጊዜው የተከሰቱትን የረሀብና የድርቅ አደጋዎችን በመከላከል በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ከርሀብና ከሞት የታደገና የወገን ደራሽ ወገን መሆኑን በተግባር ያስመሰከረ ድርጅት ነዉ፡፡

ድርጅቱ 1997 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በተጠቃሚው ሕብርተሰብ ጥያቄ ዘርፈ ብዙ የተቀናጀ የገጠር ልማት ፕሮግራሞችን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም የምግብ ዋስትና እጦት ያለባቸውንና የከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ ከጥገኝነት ተላቅቀው በምግብ ሰብል ራሳቸውን እንዲችሉና ሀብት እንዲያፈሩ፣ ጥሪት እንዲቋጥሩ አስችሏቸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ 3ኛውን የአምስት አመታት ስትራቴጅክ እቅድ (እ.ኤ.አ ከ2016 - 2020) ተግባራዊ በማድረግ ላይ ሲሆን ዓላማውን ለማሳካት ደግሞ በአራት ዋና ዋና ፕሮግራም ምሰሶዎች ላይ በማተኮር አመርቂና ዘላቂ ልማት ስራዎችን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡

አመልድ በተለይ በአካባቢና ደን ልማት፣ በውሃ ሃብት፣ሳኒቴሽንና መስኖ ልማት፣ በግብርናና የአደጋ ስጋት ቅነሳ፣ የወጣቶች ኢንተርፕራይዝና የግል ሴክተር ልማት እንዲሁም በልማት ተካታቾች (cross cutting issues) ማለትም በስርዓተ-ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት፣ኤችአይቪ/ቫይረስስርዓተ-ምግብና የአየር ንብረት ለውጥ ጋር የተያያዙ ሰፋፊ ፕሮግራሞችን 24 ለጋሽ ድርጅቶች በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ 55 ወረዳዎች 32 ሁለገብ የተቀናጀ የልማት ፕሮጀክቶችን በመተግበር 1.7 ሚሊዮን ህዝብ የሚጠጋ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡ በቀጣይም 2012 ዓ.ም መጨረሻ 3 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ አመልድ በዕለት እርዳታና መልሶ ማቋቋም እንዲሁም የተቀናጀ ዘላቂ ልማት ፕሮግራሞችን በማከናወን 35 ዓመታት የካበተ ልምድ ያለው የክልሉ ቀዳሚ መንግስታዊ ያልሆነ የልማት ድርጅት ነው፡፡

በሃብት ማሰባሰብ ረገድም ከትልልቅ ለጋሸ ድርጅቶችና አጋር አካላት በቀጥታ የልማት ፈንድ ማግኘት በመቻሉና እንዲሁም በስራ ላይ ከሚገኙት ማህበራዊ ኢንተርፕራይዞች በቀጣይ በሚገኘው ትርፍ አመልድ ራሱን ፋይናንስ ማድረግ የሚያስችለውን አሰራር የሚከተል በመሆኑ የክልሉን የልማት ጥያቄ ከዘላቂ ልማት አኳያ ትርጉም ያለው ስኬት ለማስመዝገብ በሚያስችለው ቁመና ላይ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት ካስመዘገባቸው የልማት ስራዎች መካከል በተለይም በደን ልማት ከክልሉ የደን ሽፋን ውስጥ 4 በመቶ የሚሆነውን በማከናወን የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል፡፡ ለዚህ ስራው አመልድ እ.ኤ.አ 2007 አገር አቀፍ የአረንጓዴ ጀግና ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በተጨማሪምተፋሰስ ልማቶችን በማልማት በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ በቦረቦር ማዳን እንዲሁም በብዝሃ-ህይወት ጥበቃና የተራቆተ መሬት ከንክኪ ነጻ ሆኖ እንዲያገግም በማስቻል ረገድ መልካም ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትናመስኖ ልማት በመዘርጋት አርሶ አደሩ በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ እንዲያመርትና ኑሮው እንዲሻሻል አድርጓል፡፡ በዚህም እ.ኤ.አ 2009 የአገር አቀፍ የንፁህ መጠጥ ውሃና ንፅህና አጠባበቅ ስራዎች ምርጥ አፈፃፀም ተሸላሚ ሆኗል፡፡

ከግብርና ልማትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር አኳያ አርሶ አደሮች የምግብ ዋስትናቸው እንዲረጋገጥና ስርዓተ ምግባቸው እንዲሻሻል በመደረጉ ወገኖቻችን ከድህነት እንዲወጡ አስችሏል፡፡ በተለይም በቅርቡ ከሩዋንዳ በተገኘው ሁሉን አቀፍ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ልማት የተራቆቱ ተዳፋቶችና ተራራማ ቦታዎችን መልሶ በማልማት ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል፡፡

ለአርሶ አደሩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች፣ የተዳቀሉ የፍራፍሬ ችግኞች፣ የአትክልት ዘር በማቅረብ የአርሶ አደሩ ምርታማነት ከፍ እንዲል የድርሻውን ተወጥቷል፡፡

ድርጅቱ የእንስሳት እርባታና ማድለብ ከመኖ ልማት ጋር አጣምሮ በመስራት የገበያ ትስስር እና የመንደር-ተኮር እንዲሁም የብድርና ቁጠባ ቡድኖችን በመመስረት አቀናጅቶ በሚያክናውናቸው ስራዎች ተጠቃሚዎች በኑሯቸው እንዲለወጡና ጥሪት እንዲኖራቸው እየተደረገ ነው፡፡

አመልድ ባከናወነው ውጤታማ የዘላቂ ልማት እንቅስቃሴዎች የህዝቡን የአኗኗር ዘይቤ የቀየረ ሲሆን ብዙዎችን ከምግብ ዋስትና ተረጅነት አውጥቷል፡፡ በአጠቃላይ በድርጅታዊ ስኬታማ የፕሮግራምና ፕሮጀክት የአመራር ብቃቱ 4ኛውና 6ኛው አገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ውድድር እንዲሁም በአለም-አቀፍ ደረጃ ከአውሮፓ የጥራትና ምርምር ማኅበር የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል፡፡

አመልድ በቀጣይ አመታት ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር ያለንን አጋርነት ማጠናከር ይኖርብናል፡፡ በቀጣይም አብረውን ሊሰሩ የሚችሉ አዳዲስ ድርጅቶችን መጋበዝ ይገባናል፡፡ በድርጅቱ የተቋቋሙ የገቢ ማስገኛ ኢንተርፕራይዞችንም እንዲሁ ውጤታማ በማድረግ የሚገኘውን ገቢ አመልድ ራሱን ፋይናንስ የሚያደርግበትን ሁኔታ መፍጠር አለብን፡፡ በመሆኑም ፕሮጀክቶቻችን የክልሉን ልማት በዘላቂነት በመደገፍ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ይደረጋል፡፡

ከዚህ ባሻገር ድርጅቱ የሚያከናውናቸውን የልማት ስራዎች በገንዘብ፣ ቁሳቁስና ስልጠና እየደገፋችሁ እዚህ ላበቃችሁት ለጋሽ ድርጅቶች፣ የመንግስት አጋር አካላትና መላውን ህዝብ በአመልድና በተጠቃሚው ህብረተሰብ ስም ላመሰግን እወዳለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

Last Updated (Tuesday, 09 July 2019 11:52)

 
ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today3
Week118
All79216

Currently are 27 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?